Admin1
Mon, 07/27/2026 - 15:40
ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ የክብር እንግዶች በፋብሪካው ግቢ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ
(ዱራሜ፣ ሐምሌ 11/2018 (ሀድያ ዞን ኮሙኒኬሽን) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ የ"ዓለም ፒፒ የፕላስቲክ ከረጢት ማምረቻ ፋብሪካ"ን በይፋ መርቀው የከፈቱት የክብር እንግዶች በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ውስጥ ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራ አኑረዋል።
በዛሬው ዕለት ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ተገንብቶ የተመረቀውን ማምረቻ ፋብሪካ የምረቃ ስነ-ስርዓት ተከትሎ፣ የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በጋራ በመሆን የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩን አከናውነዋል።
ይህም ፋብሪካው ከሚያበረክተው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባሻገር፣ ሀገራዊውን የአረንጓዴ አሻራ የልማት ስራ የሚደግፍና ለዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ ከፍተኛ ትኩረት መሰጠቱን የሚያሳይ መሆኑ በስነ-ስርዓቱ ላይ ተመላክቷል።