Skip to main content
006
የአምራች ኢንዱስትሪዎችና አገልግሎት መስጫ ተቋማት የአካባቢ ብክለትን መከላከል እንደሚገባቸው ተገለጸ፦
(ዱራሜ ፣ ሰኔ 03/2018) ፣በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ደን አከባቢ ጥበቃ እና ልማት ቢሮ ''ብክለትን እንቀንስ፣እንከላከል'' በሚል መሪ ቃል ከአምራች ኢንደስትሪዎች፣አገልግሎት ሰጭ ተቋማት፣ከሀይማኖት መሪዎች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በህግ ማስከበር ዙሪያ ትኩረት ያደረገ የውይይት መድረክ በሆሳዕና ከተማ አካሂዷል ።
በዚሁ ወቅት አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ አገልግሎት መስጫ ተቋማት በክልሉ ከኢንዱስትሪ ከሚወጡ አካባቢ በካይ ተረፈ ምርትና በሌሎች የብክለት መንስዔዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማካሄዱ ወሳኝ መሆኑ ተነስቷል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ደን አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሃም መጫ ከመምረቻ የሚወጡ ጭሶች ከአየር ብክለት ባለፈ በመሬት ምርትና ምርታማነት ላይም ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑን አብራርተዋል ።
ኃላፊው ከአምራች ኢንዱስትሪ የሚወጡ የብክለት አምጭዎች በግብርናው ዘርፍ የምግብ ዋስትና እንዳይረጋገጥ ከፍተኛ ተግዳሮት ሆኖ እንደቆየ አመላክተው በዘርፉ የህግ ማስከበር ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል ።
በመድረኩ ከክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ ከወሃና ማዕድንና ኢነርጂና ከኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮዎች የተውጣጡ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት መሪዎችና የአምራች ኢንዱስትሪና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ባለቤቶች ተገኝተዋል ።